Monday, December 30, 2013

ሰጥቶ ነፃነት የተከለከለ ህዝብ ( ሽሬ )



(የአረናን ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ የተከለከሉ የሽሬ ነዋሪዎችፎቶ ከአብርሃ ደስታ)

ሽሬ ከመቀሌ በስተ ሰሜን ምዕራብ 320(?) ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ ከተማ ናት። በአውቶቡስ ጉዞ ከሰባት እስከ ስምንት ሰዓት ይወስዳል (እኛ ስምንት ሰዓት ፈጅቶብናል) ከመቀሌ ማይመኽደን፣ አጉላዕ፣ ዉቅሮ፣ ነጋሽ፣ እንዳተካ ተስፋይ፣ ፍረወይኒ (ስንቃጣ)፣ማይመገልታ፣ እዳጋሓሙስ፣ ዓዲግራት፣ አሕዘራ፣ ሴሮ፣ እንትጮ፣ ማርያም ሸዊቶ፣ ዓድዋ፣ አክሱም፣ ዉቅሮማራይ፣ ሰለኽለኻ አቋርጠን ሽሬ እንዳስላሴ ገባን።
ሽሬ ለም መሬት ነው። ሰፊና ሜዳማ የእርሻ መሬት አለ። ህዝቡ እንግዳ አክባሪ ነው። ሽሬ የሆነ ደስ የሚል ነገር አለው። ግን ባከባቢው ብዙ ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሉ። ይሄን ጉዳይ ሌላ ግዜ እመለስበታለሁ። አሁን ግን ወደ የስብሰባው ጉዳይ እንግባ።
ዓረና መድረክ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት ወሰነ። ስብሰባው የሚያዘጋጅ የዓረና ቡድን ወደ ከተማው ተላከ። በከተማው ስብሰባ ለማድረግ የሚያስችል ፍቃድና መሰብሰብያ አዳራሽ እንዲሰጠን ጠየቅን። ከአንድ ቀን በኋላ ስበሰባ ማድረግ እንደምንችል ፈቅደው አዳራሽ ግን እንደተያዘ ነገሩን። አዳራሽ መከራየት እንደምንችል ካልሆነ ደግሞ በሆነ ሜዳ ማካሄድ እንደምንፈልግ ነገርናቸው። ከአንድ ቀን በኋላ ተነጋግረው አዳራሽ ፈቀዱልን (ሜዳ ላይ ስብሰባ ከተደረገ ለነሱ ጥሩ አለመሆኑ ያውቁታል)
አዳራሽ ካስፈቀድን በኋላ ሓሙስና ዓርብ ቀሰቀስን። ከአስር በላይ በራሪ ወረቀት ተበተነ። በማይክሮፎን ተጠቅመን መረጃው ለህዝብ አዳረስን። የከተማው ካድሬዎች በእግርና በመኪኖች እኛን እየተከታተሉና የሽሬ ህዝብ ለኛ ያለው ስሜት ይሰልዩ ነበር። ያኔ ካድሬዎቹና ሰላዮቹ በኛ ላይ ያደረሱት ምንም ተፅዕኖ አልነበረም። የተቀደደብን ወረቀትም ጭራሽ አልነበረም (በሌሎች አከባቢዎች ካድሬዎቹ ወረቀት ተቀብለው የሚቀዱ ነበሩ) ዓርብ ቤት ለቤት ቀሰቀስን።
ካድሬዎቹና ሰላዮቹ የህዝቡን ጥሩ አቀባበል ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት አደረጉ። ዓርብ ከሰዓት የከተማው የካቢኔ አባላት ተሰብስበው በጉዳዩ ተወያዩ። ዓርብ ማታ (ከምሽቱ አንድ ሰዓት) የከተማው ከንቲባ አቶ መረሳ አታክልቲና ምክትል ከንቲባው መምህር ሃይለ አዳነ ወደ ማዘጋጃቤት ጠርተው ቅስቀሳ ማቆም እንዳለብን ነገሩን። ስላደረግነው ቅስቀሳ በቂ መረጃ መሰብሰባቸው፣ በጉዳዩ ካቢኔ መሰብሰቡና እስካሁን የተደረገ ቤት ለቤት ቅስቀሳ በቂ መሆኑ መግባባት ላይ መደረሱ ተነገረን።
እኛም ተቃወምን። አቶ አስገደ ገብረስላሴ ደግሞስለ ቅስቀሳው በቂነት የምናውቀውና የምንወሰነው እኛ ራሳችን እንጂ እናንተ አይደላችሁም። ስለዚህ ቅስቀሳችን እንቀጥላለንአለ። ምክትል ከንቲባው በጣም ተናዶአንደኛ ስትቀሰቅሱ መሳደብ አቁሙአለ።መቼ ነው የተሳደብነውስለውግዕዙይ ምምሕዳርብላችኋል አለኝ። ለካ በማይክሮፎን ስንቀሰቅስ የስብሰባው አጀንዳዎች እንዘረዝር ነበር። ከአጀንዳዎቹ አንድ ስለመልካም አስተዳደር እጦትና መፍትሔውየተመለከተ ነበር። በትግርኛግዕዙይ ምምሕዳርን መፍትሒኡንይላል። አስገደም አስከትሎግዕዝይናኮ ሙስና ነው። ስለ ሙስና እንነጋገራለንአለ (ሙስና በትግርኛ ግዕዝይና ነው) ምክትል ከንቲባውምታድያ ሙስናኮ መንግስታችን ህወሓት እየተታገለው ነው ያለው፤ እናንተ ምን አገባቹአለ።
ርእሱ ለመቀየር ሞከርኩ።እስከ ስብሰባው ቀን ድረስ ብንቀሰቅስ ችግሩ ምንድነውብዬ ጠየቅኩ። ከንቲባውአንደኛ ህዝቡ በቅስቀሳው ደስተኛ አይደለም፤ ሊረብሽ ይችላል። ሁለተኛ ነገ ቅዳሜ ነው፤ የገበያ ቀን ነው። ሦስተኛ እስካሁን በቂ ቅስቀሳ ተደርጓልየሚሉ ሦስት ምክንያቶች አቀረበ። እኛም ለሦስቱ ምክንያቶች መልስ ሰጠን።አንደኛ ህዝቡ አይረብሽም፤ በጥሩ ሁኔታ ተቀብሎናል። ሁለተኛ በሕጉ መሰረት ከገበያ ቦታ አምስት መቶ ሜትር ርቀን ነው የምንቀሰቅሰው። ሦስተኛ እኛ በፈለግነው ግዜ ቅስቀሳው እንጀምራለን፣ እናቆማለንአልን።
ቅስቀሳው ማቆም እንዳለብን፣ የካቢኔ ዉሳኔና ትእዛዝ መሆኑ ነገሩን። ትእዛዝ ከሆነ በፅሑፍ እንዲያሳውቁን ጠየቅን። በፅሑፍም አሳወቁን። ፅሑፉ ለሚደርስብን ችግር የከተማው አስተዳደር ሐላፊነት እንደማይወስድ ይጠቁማል። ፀጥታ የማስከበር ሐላፊነት የመንግስት ተግባር ነው፤ የኛ ስራ አይደለም ብለን ቅዳሜም ቅስቀሳችን ቀጠልን። ምንም ችግር አልደረሰብንም።
እሁድ ጠዋት በተፈቀደልን አዳራሽ አከባቢ በማይክሮፎን ህዝቡን ስለ ስብሰባ ማስታወስ ጀመርን። መቀስቀስ እንደሌለብን ፖሊስ ነገረን (ፖሊስ ቅስቀሳው ለማስቆም መታዘዙ ነግሮናል) መቀስቀሱ አቁመን ወደ አደራሹ ሄድን። ከሁለት ሰዓት ጀምሮ ብዙ ሰዎች ተሰባስበዋል። አደራሹ ግን ዝግ ነው። ዘበኛው እንዲከፍትልን ጠየቅን።አልታዘዝኩምአለ። ከድር ወደተባለ አለቃው ደወልኩ። አዳራሹ መክፈት እንዳለበት ነገረው። ባደራሹ በር ሁለት ሰዎች አሉ።ጥብቃ ነንአሉ። ግን የህወሓት ካድሬዎች ናቸው።
በሩ ተከፈተ። ህዝብ ለመግባት በር ላይ ሲደርስ ሁለቱ ካድሬዎች ወደ አደራሹ የሚገባ ሰው የቀበሌ መታወቅያ በእጁ የያዘ ብቻ መሆኑ አወጁ። ህዝቡምመታወቅያ አናሳይምአለ።መታወቅያ ካላሳያቹ አትገቡምተባለ። ጭቅጭቅ ተጀመረ።በህዝብ ስብሰባ ለመሳተፍ መታወቅያ አያስፈልግምብዬ ለሁለቱም ካድሬዎች ነገርኳቸው።መታወቅያ ያስፈልጋል ተብሏልአሉኝ።ህዝቡ መፈተሽ ያለበትኮ ፖሊስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምአልኳቸው። ካድሬዎቹ የአዳራሹ በር ዘጉት።
ወደ ከንቲባው ደውዬ ህዝብ በፖሊስ ብቻ እየተፈተሸ፣ የቀበሌ መታወቅያ ሳይጠየቅ እንዲገባ ለማድረግ ሕጋዊ ፖሊስ እንዲመደብልን ጠየቅኩት። እሱም ፖሊስ እንደማይመድብ፣ የቀበሌ መታወቅያ ያለው ብቻ መግባት እንዳለበትም ነገረኝ። እኔም እንደዛ ከሆነ ስብሰባው ከአዳራሹ ዉጭ እንደምናደርገው ነገርኩት።አይሆንምአለኝ።
መታወቅያ ያልያዘ አይገባምስለተባለ ስብሰባው ባደራሹ በር ለማድረግ ተስማማን (ልብ በሉ የከተማው አስተዳደር ፖሊስ እንደማይመድብና ለሚፈጠረው ችግር ሐላፊነት እንደማይወስድ ነግሮናል) አደራሽ ዉስጥ ገብቶ የነበረ ሰው እንዲወጣ አደረግንና ስብሰባው ባደራሹ በር አከባቢ ባለው ሜዳ ጀመርን። በጣም ብዙ ህዝብ ነበር (በሺዎች የሚቆጠር)
የከተማው አስተዳዳሪዎች መጡ (ከንቲባው፣ ምክትል ከንቲባው፣ የፕሮፓጋንዳ ሐላፊውእስከ ቀበሌ ተጠሪዎች ተሰባስበው መጡ። ስብሰባው ማቋረጥ እንዳለብን ነገሩን። ከፈለጋቹ እሰሩን እንጂ ህዝብ ጠርተንማ ስብሰባ አናቋርጥም አለን። እኛ ከከተማው አስተዳዳሪዎች ጋር እንጨቃጨቃለን። የዓረና ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ በርሀ ግን ንግግር ማድረግ ጀመረ። አለመግባባቱ ግን እየከረረ መጣ። ባከባቢው ደንብ የለበሰ ፖሊስ አልነበረም። የደህንነት ሰዎች ግን መዓት ነበሩ።
አንድ የፖሊስ አዛዥ መጣ።ስርዓት ያዙአለን።ስብሰባ እያካሄድን ነንአልን።እዚህ ስብሰባ እንድታደርጉ አልተፈቀደላችሁምአለ (ትክክል ነበር፤ በሜዳ ስብሰባ ለማድረግ አልተፈቀደልንም)ግን ህዝቡ በካድሬዎች ወደ አዳራሽ እንዳይገባ እየተከለከለ ነውብለን ለፖሊሱ ነገርነው። ፖሊሱአሁን ወደ ተፈቀደላቹ አዳራሽ ግቡሲለን ህዝቡ ለመግባት ሰልፍ ያዘ።
ህዝቡ መታወቅያ እየተጠየቀ ነውብለን ለፖሊሱ አሳወቅን። (ከከንቲባውና ጓደኞቹ ጋር የምናደርገው ንትርክ ግን እየከረረ ነው) ፖሊስመታወቅያ አያስፈልግም። እየፈተሻቹ አስገቡትአለ። ከንቲባውያለ መታወቅያማ ሰው አይገባምአለ። ፖሊሱና ከንቲባው ተጨቃጨቁ። ከንቲባው ተቆጣው። ከዛ ፖሊሱ እኛንና የህወሓት አባላትን መሸምገል ጀመረ። አስገደ ገብረስላሴአትረብሹንአለ (አስገደ ተናዶ ነበር) መታወቅያ የያዘ ብቻ ሰልፍ ስይዝ መታወቅያ ያልያዘ ጥግ ያዘ። አንድ የደህንነት ሐላፊ ነው የተባለው ሰው መጥቶ ለሚፈት ካድሬዎችየቀበሌ መታወቅያ ያለው ሳይሆን የዓረና መታወቅያ ያለው ብቻ ነው የምታስገቡየሚል ትእዛዝ አስተላለፈ።
ስብሰባው የህዝብ እንጂ የዓረና አባላት ብቻ አይደለምአልኩና ሁኔታው በፌስቡክ ለመዘገብ ወደ ኢንተርኔት ካፌ ገባሁ። በአደራሹ በር አከባቢ የተሰበሰው የሽሬ ከተማ ህዝብ ለመበተን ጥረት እያደረጉ ነበር እነ አቶ ከንቲባ። ግን በጣም ብዙ ስለነበር በቀላሉ መበተን አልተቻለም። እንዳውም ጭቅጭቁ ለምስማት ይጠጋ ነበር።
ከደቂቃዎች በኋላ ተመለስኩ። አቶ አስገደ ገብረስላሴ ፎቅ ላይ ወጥቶ በማይክሮፎን መናገር ጀመረ።የሽሬ ህዝብ ታፍነሃል…’ ምናምን ይላል። ከዞኑ ፅሕፈት ቤት ሦስት ሰዎች በፍጥነት ጮክ ብለው እየተናገሩ ወደ ተሰበሰው ህዝብ ተቀላቀሉ። የከተማው አስተዳዳሪዎችና ተጠሪዎች እንዲሁም የደህንነት ሰዎች አሰባስበው አስር ዓመት የማይሞላቸው ህፃናት አስከትለውአሉ። እየጮሁ ዓረናና የዓረና አባላትን መሳደብ ጀመሩ።ዓረና ሻዕቢያ ነው! ዓረና ኪራይ ሰብሳቢ ነው! ዓረና አሸባሪ ነው! እያሉ ይጮኃሉ።
አስገደ ገብረስላሴ ፎቅ ላይ ሁኖ ይናገራል። የሚናገረውን ነገር ህዝቡ እንዳይሰማው ለማድረግ ድምፅ እየጨመሩአስገደ ሌባእያሉ መጮህ ተያያዙት። ለስብሰባ የመጣ ህዝብ ተበተነ (ጥጉ ጥጉ ያዘ) አከባቢው እነሱ ብቻ ተቆጣጠሩት። ፎቅ ላይ ሁነን ቪድዮ ለማንሳት ሞከርን። መጨረሻ እየጮሁ ወደ ዞን አስተዳደር ህንፃ ገቡ። ስብሰባው ተስተጓጎለ።
ረብሻው ይመሩት የነበሩ ሦስት ሰዎች ሲሆኑ ሁለቱ ተፈናቃይ ኤርትራውያን (ግን በማዘጋጃቤት የተቀጠሩ) አንድ የደህንነት ሐላፊ ናቸው። ግን ለምንድነው ኤርትራውያን ለህወሓት የሚደግፉ? የሽሬ ህዝብ ህወሓትን ያልደገፈ አርትራውያን ለምን? የሽሬ ህዝብ ግን በሁኔታው እጅግ መገረሙ ከሠዓት በኋላ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።
ስብሰባው ተጀምሮ ተስተጓጎለና ወደ ቢሮአችን አመራን። ህዝቡአይዟቹይለን ነበር። ከዛ እኔ ወደ ዓድዋ አመራሁ። የማገኛቸው የዓረና አባላት ለማደራጀት ነበር። ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓድዋ ነበርኩ። ዓድዋ ሁኜ ስለ የሽሬ ስብሰባ ለመፃፍ ፈለግኩ። ግን ደክሞኝ ነበር። የተወሰነ መረጃ ለመስጠትና ዓድዋ ከተማ እንደምገኝ ለማሳወቅ ትንሽ ፃፍኩኝ። ግን እንተርኔት ደካማ ስለነበር ፖስት ማድረግ አልቻልኩም። ፅሑፉ ግን በፍላሽ ይዠው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ ወደ መቀሌ ጉዞ ጀመርኩ። ከምሽቱ ሦስት ሰዓት መቀሌ ገባሁ። ዓድዋ ሁኜ የፃፍኩት በመቀሌ ከተማ ለጠፍኩት። ለካ ፅሕፉዓድዋ ነኝ ያለሁትየሚል አለው። (ልብ አላልኩትም ነበር። ያስታወስኩት አሸናፊ የተባለ ጓደኛዬ ሲነግረኝ ነው። ደክሞኝ ነበር። ድካሙ አሁንም አልወጣልኝም)
የምጥሰጠን መረጃ ታማኝ ከሆነ ለምን በፎቶ ወይም ቪድዮ አታስደግፈውምየሚሉ አስተያየቶች ይነሳሉ። ግን ፎቶ ወይም ቪድዮ የማልለጥፍበት ወይ የማላነሳበት ምክንያት አለኝ። በውቅሮ ከተማ ስብሰባ ስናደርግ ካድሬዎች ህዝብ በስብሰባው እንዳይሳተፍ ይመልሱ ነበር። ካድሬዎቹ ህዝብ ሲመልሱ በካሜራ እንቀርፃቸው ነበር። ባጋጣሚ ግን የከተማው ፖሊስ ኮማንደር ሰው ሲመልስ ቀረፅነው (ከሌሎች ካድሬዎች ጋር) የፖሊስ ኮማንደሩያለ ፍላጎቴ ቀርፀውኛልብሎ ፖሊስ ጣብያ ወሰደን። ካሜራው በፖሊስ ተያዘ። አባሎቻችን ተንገላቱ፣ የተቀረፀ ቪድዮ አጠፉት፣ በዛ ሂደት የዉቅሮ ስብሰባችን ሳንቀርፀው ቀረን።
ከዉቅሮ ትምህርት ወስደን ቀረፃ የምናካሂድ በስብሰባው አዳራሽ ዉስጥ ብቻ ነው። በማይጨው ከአደራሽ ዉጭ አልቀረፅንም። በተምቤን ካድሬዎቹ በአደራሹ በር አከባቢ ተሰፍስፈው ሲያስቸግሩን በሞባይል የምቀርፃቸው መስዬ ባከባቢው አለፍኩ። የተቀረፁ የመሰላቸው የዓብይ ዓዲ ከተማ ፖሊስ ኮማንደር (ክብሮም) ሌሎች ባለስልጣናት ወደ ፖሊስ ጣብያ ወሰዱኝ።ያለ ፍቃዳችን ቀረፅከንአለኝ።አልቀረፅኩምብዬ ሞባይሌን በባለሙያ ተፈተሸ። ምንም አልቀረፅኩም። ተለቀቅኩ።
ከዚህ በመነሳት በሽሬም እንዳያስተጓጉልን በመስጋት ከአዳራሽ ዉጭ ቪድዮ ለመቅረፅ ይሁን ፎቶ ለማንሳት አልፈለግንም ነበር። ግን ስብሰባው መስተጓጎሉ ከተረዳን በኋላ ግን ሁኔታው በቪድዮ ቀርፀነዋል፣ ፎቶም አንስተናል። የነበረን ሐሳብ ግን ስብሰባው ተጀምሮ የሚካሄደው ዉይይት ለመቅረፅ ያለመ ነበር። የተሳታፊዎች ፍቃድ ከሆነ ማቅረብ እችላለሁ። በሚቀጥለው መታወቅያ ያልያዙ ሰዎች ጥግ ይዘው ሲጠባበቁ የሚያሳይ ነው።
ባጠቃላይ በሽሬ ያደረግነው ቅስቀሳ ዉጤታማ ነበር። ስብሰባው (ተጀምሮ ሳያልቅ) በድል ተጠናቋል ማለት ይቻላል። ህወሓቶች ግን የህዝቡ የተቃውሞ መንፈስ በጣም አስደንግጧቸዋል። ሁሉም በስብሰባው እንዲሳተፍ ቢፈቀድለት ኑሮ ወደ ሁለት ሰው ይሳተፍ ነበር የሚል ግምት አለን። ግን ብዙ መስዋእት የከፈለ ህዝብ አማራጭ ሐሳብ እንዳይሰማ ተነፈገ። የፈለገውን ሐሳብ በነፃነት እንዳያራምድ ተደረገ። ህዝብ አማራጭ ሐሳብ እንዳይሰማ መከልከል ህዝብን ማፈን ነው። ታድያ ህዝብ እንዲህ ከታፈነ ለምን ነበር ይህን ሁሉ መስዋእትነት የከፈለው? የሽሬ ህዝብ ደሙ የሰጠ ለነፃነቱ አልነበረም እንዴ? ደም የሰጠ ህዝብ ነፃነት ይከለከላል?
ለማንኛውም የሽሬ ህዝብ የካድሬዎችን ማስፈራርያ ሳይበግረው በስብሰባው ለመሳተፍ መጥቷል። ህዝቡ በስብሰባው እንዳይሳተፍ የተደረገው በማስፈራራት ሳይሆን የአደራሹን በር በመዝጋትና ስብሰባው እንዳይካሄድ በመረበሽ ነበር። ህዝቡ ግን ለውጥ ይፈልጋል። በቅስቀሳው ወቅት ብዙ አባላት አፍርተናል። ስብሰባው ቢካሄድ ኑሮ ደግሞ የበለጠ ይሆን ነበር። በሐሳብ መከራከር የሰለጠነ መንገድ ነው። ህወሓቶች ዓቅም ካላቸው በህዝብ ፊት ቀርበው ከኛ ጋር ይከራከሩ። ስብሰባ መረበሽ ጀግንነት አይደለም። ጀግንነት ተከራክሮ ማሸነፍ ነው።
በትግራይ ሙሉ በሙሉ አሸንፌያለሁ የሚል መንግስት እንዴት በዓረና ስብሰባ ይደነግጣል? ህወሓት የህዝብ ድጋፍ ካለው ለምን ዓረና ከህዝብ እንዳይገናኝ እንቅፋት ይፈጥራል? ህወሓት ዓቅም እንደሌላቸው አረጋግጠዋል። በሽሬ ከተማ ህወሓት ምንም ድጋፍ እንደሌለውም አረጋግጠናል። የሽሬ ህዝብ በጣም የተበደለ ነው።

ይህን ሁሉ መስዋእትነት በነፃነት የመሰብሰብ መብት ካላስገኘ ታድያ ፋይዳው ምንድነው? ህወሓት የትግራይ ህዝብ ድጋፍ አለኝ ብሎ የሚያምን ቢሆን ኑሮ ይህን ያህን አይፈራም ነበር።

  አብርሃ ደስታ ከመቀሌ
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/11392

No comments:

Post a Comment