Sunday, December 29, 2013

ቴዲ አፍሮ ለአድናቂዎቹ ስለተሳሳተው የመጽሔት ቃለምልልስ ምላሽ ሰጠ


በሃገር ቤት የሚታተመው እንቁ መጽሔት የቴዲ አፍሮን ቃለምልልስ በተሳሳተ ርዕስ ማውጣቱን ተከትሎ በርካታ ውዝግቦች ተከስተው ቆይተዋል። መጽሔቱ እርማት የሰጠ ቢሆንም አንዳንድ ወገኖች ግን የተሳሳተውን የመጽሔት የሽፋን ገጽ በማየት መነጋገሪያ አድርገውት ቆይተዋል። ቴዲ በዚህ ጉዳይ ላይ ለአድናቂዎቹ በፌስቡክ ገጹ በአማርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋ ምላሽ ሰጥቷል። እንደሚከተለው ይነበባል።
ለሙዚቃ አፍቃሪዎቼ በሙሉ
ከጥቂት ሳምንት በፊት የዳግማዊ ሚኒሊክን መቶኛ አመት የሞት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በእንቁ መጵሔት ተጋብዤ ቃለ ምልልስ አድርጌአለሁኝ። ይሀዉ ዉይይታችን አመጣጡን ያየ አካሄዱን ያዉቃልእርዕስት ስር ለህዝብ እንደቀረበ አዉቃለሁ። ከዚህ ዉጪ እኔ በማላዉቀዉ ሁኔታ መፅሔቱ በሰራዉ ስህተት ፎቶዬን በሌላ አነጋገር አጅቦ ያወጣዉ ከኔ እምነትም ሆን ጉዞ ጋር የሚራመድ ጉዳይ አይደለም። ይህንኑ ለማረጋገጥአመጣጡን ያየ አካሄዱን ያዉቃልበሚል ርዕስ ስር በወጣዉ መፅሔት መልክቶቼን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል። ያም ሆኖ መፅሔቱ በሰራዉ ስህተት እርምት አድርጎ ይቅርታም ጠይቆናል። ጉዞዬ የፍቅር የአንድነት እና የይቅር ባይነት ነዉና ይህንንም ጉዳይ በዚሁ ስሜት ውስጥ እናስተናግደዋለን።

ፍቅር ያሽንፋል!


ቴዎድሮስ ካሳሁን

No comments:

Post a Comment