Friday, December 27, 2013

በጎንደር ዳባት ሕጻን ሰለሞን ላይ ማን የጥይት እሩምታ አወረደበት?



ሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ነዋሪ የነበሩት 55 ዓመቱ አቶ ማስረሻ ጥላሁን የተመሰከረላቸው አርሶ አደር ገበሬ በመሆናቸው የክልሉ ግብርና /ቤት ሞዴል አርሶ አደር በማለት ሸልሟቸዋል፡፡የሁለት ወንድና የአምስት ሴት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ማስረሻ ወሰኔን ገፍተሃል የሚል ክስ ቀርቦባቸው በዳባት ፍርድ ቤት 300 ብር መቀጮ ተጥሎባቸው በመክፈል ወደ እርሻቸው ቢመለሱም የገበሬ ቀበሌ ማህበሩ ሊያስቀምጣቸው አልቻለም፡፡
ጥቅምት 15/2006. ከሁለተኛ ልጃቸው ሰለሞን ማስረሻ ጋር አትክልት ተክለው አመሻሹ ለይ ተዳክመው መኖሪያ ቤታቸው ገብተዋል፡፡ማለዳ 1200 ከመኝታው ባላቋረጠው የውሾች ጩህት ከእንቅልፉ ተነሳው ሰለሞን በሩን ከፍቶ ሲወጣ የጥይት እሩምታ ይወርድበታል፡፡አባት ልጄን ብለው የሌሊት ልብሳቸውን እንደለበሱ ወደ ውጪ ሲወጡ የጥይቶቹ አቅጣጫ ወደ እርሳቸው በመዞሩ ማን እንደተኮሰባቸውና ማን እንደመታቸው ለማየት እንኳን ሳይታደሉ ይህችን ጨካኝ አለም ተሰናበቱ፡፡
መኖሪያ ቤቱ ላይ በሚወርደው የጥይት እሩምታ የተነሳ ሁለት ላሞችና አንዲት ጊደር ተገደሉ፡፡የስምንት አመቷ ስለእናት ማስረሻ ቀኝ እጇ ላይ በጥይት ተመታች፡፡ባለቤታቸውን በሞት የተነጠቁትና ምንም የማታውቀውን ህጻን ልጃቸውን አካለ ጎደሎ ያደረገባቸውን ጥይት ማን እንደተኮሰው ለማወቅ ለዳባት ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አቤት ሲሉ ‹‹ባለቤትዎ ሽፍታ መረጃ ስለደረሰን ግድያውን የፈጸመው የጸረ ሽብር ግብር ሃይል ነው››ተብለዋል፡፡‹‹ሽፍታ እንዴት ባለ80 ቆርቆሮ ቤት ይሰራል?ልጆቹን ያስተምራል?ሞዴል አርሶ አደር ተብሎ ይሸለለማል?በየት አገር በብአዴን ስብሰባ ላይ እንድትገኝ ተብሎ በደብዳቤ ይጠራል?እንዴት ሽፍታ የመለስ ዜናዊን አደራ ለመወጣት በምንችልበት ሁኔታ ለመወያያት እንድንነጋገር ይባላል? ›› ጥያቄዎቹን ፖሊሶቹ ሊመልሱላቸው ባለመቻላቸው ወደ ክልሉ አስተዳደር አምርተዋል፡፡ክልሉ ለዞኑ ዞኑ ለወረዳው ደብዳቤ እየጻፈ እስካሁን ድረስ የአቶ ማስረሻ እውነተኛ የግድያ መንስኤ መታወቅ አልቻለም፡፡




No comments:

Post a Comment