Sunday, December 22, 2013

የአማራ ዴ/ኃ/ን ለሱዳን ተላልፎ በተሰጠው መሬት ዙሪያ “ዳሩ ካልተጠበቀ መሃሉ ዳር ይሆናል” የሚል መግለጫ አወጣ


ጋዜጣዊ መግለጫ 
ዳሩ ካልተጠበቀ መሃሉ ዳር ይሆናል”!!
ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የተሰጠ መግለጫ
ታህሣሥ 10 ቀን 2006 ..
በዓለም ላይ እስከአሁን የተከሰቱ መንግሥታት (ቅኝ ገዥዎችን ጨምሮ) ጨቋኝ (አምባገነን) በዝበዥ፣ ዘራፊ (በሙስና የተዘፈቀ) … ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። አሁን ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ እንዳለው የትግሬ ዘረኛ ቡድን የሚገዛትን ሀገርና ሕዝብ የሚጠላና ሀገሩንም ለማጥፋት 24 ሰዓት የሚሠራ መንግሥት ግን እስከ አሁን በታሪክ አልታየም። ወደፊትም ከወያኔ በስተቀር የሚገዛትን ሀገር፣ ታሪኳንና ሕዝቧን የሚጠላና ሆን ብሎ ለማጥፋትም ቀንተሌት የሚጥር መንግሥት በምድር ላይ ይከሰታል ብለን አናምንም። ይህ የትግሬ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን መጥላቱን የሚያሳይ የድርጊቱን ሥንክሣር መዘርዘር ቢቻልም፣ በአሁኑ ሰዓት የተከሰቱ ሁለት ታላላቅ ብሔራዊ ጉዳዮችን ብቻ እንኳ ብናይ ዘረኛው ቡድን ምን ያህል የሚገዛትን ሀገርና ሕዝቧን አምርሮ እንደሚጠላ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፦
  1. በሣዑዲ አረቢያ የወገኖቻችን ደም  በግፍ ሲፈስስ፣ እህቶቻችን ያለርህራሄ በቡድን ሲደፈሩ፣ 21ኛው /ዘመን በሰው ልጅ ላይ የፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ ኢሰብአዊ ግፍ ሲፈፀምባቸውና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ላይ ብሔራዊ ውርደት ሲደርስ የትግሬው ዘረኛ ቡድን የሣዑዲ አረቢያ መንግሥት በሀገሩ ላይ ይህንን ማድረግ መብቱ ነው ነበር ያለው።
  2. በዚህ ሰቅጣጭ ሐዘን ውስጥ ተውጠንና በስቃይ ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ለመርዳት ላይ ታች በምንልበት ጊዜ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳው የትግሬው ዘረኛ ቡድን አባቶቻችን ደማቸውን በማፍሰስና አጥንታቸውን በመከስከስ ጠብቀው ያቆዩትን 1600 / ርዝመትና 20-60 / ወደ ኢትዮጵያ ጥልቆ የሚገባውን ከሱዳን የሚያዋስነውን ድንበራችንን በሕገወጥነት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ፈርሞ ለሱዳን አስረከበ። ምንም እንኳን በሚስጥር ሊይዘው ቢሞክርም የድንምበር ማካለሉ ከጥር ወር 2006 እስከ መስከረም 2007 ችካል በመቸከል እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ይህንን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ የሚደረግ ሕገወጥ የድንበር ክለላ አጥብቆ መቃወምና ማውገዝ ብቻ ሳይሆን እንዳባቶቹ ደሙን አፍስሶና አጥንቱን ከስክሶ ታሪካዊ ድንበሩን ለማስከበር ቆርጦ ተነስቷል። ባንዳ የባንዳ ልጆች ከአባቶቻቸው የወረሱትን ሀገር የማጥፋትና የመሸጥ ውርስ ተግባራዊ ሲያደርጉ እኛ የአርበኛ ልጆች ነን የመንል ይህንን ደባ ዝም ብለን ብንመለከት ድንበር ላይ የተከሰከሰው የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይዎጋናል። በመሆኑም በአካባቢው ያላችሁ ታጋይ ኃይሎችና የገፈቱ ቀማሽ የሆንከው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በርስቱና በሚስቱ ያልሞተ ወንድ ልጅ ወንድ አይደለምና ወንድ ልጅ ነኝ ያልክ ሁሉ ተባበረን፣ ከዚህ በላይ የሞት ሞት የለምና።
አዴኃን ይህንን ድርጊት አምርሮ የሚቃወመው እንዲያው በጭፍኑ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ሕጋዊ የሆነ ድንበር አይኑራት ብሎ አይደለም። የድንበር ስምምነቱ ኢትዮጵያን ጎድቶ ሱዳንን የሚጠቅም፣ 110 ዓመታት በፊት የፈረሰና ሕጋዊ ያልሆነ ውልን መሠረት ያደረገ፣ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን ጥናትና ውትወታ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ  ሕዝብ ጀርባ በደባና በሕገወጥነት የተፈረመ ውል በመሆኑ እንጅ።
በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረገው የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴና ከዚያ በፊትም ጥናት ያደረጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሑራን እንደሚሉን ከሆነ ይህ ዛሬ የትግሬው ዘረኛ ቡድን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ለተፈራረመው ውል ዋቢ የሚያደርገው ውል በዳግማዊ አፄ ምኒልክና በጊዜው የሱዳን ቅኝ ገዥ በነበረችው እንግሊዝ መካከል የተፈረመው .. 1902 ነበር። አፄ ምኒልክ ይህንን ውል የፈረሙት በኃይል ተገድደውና በይዞታቸው ሥር የነበሩ ብዙ መሬቶችን ለቀው ነበር። በዓመቱ 1903 የእንግሊዙ የጦር መኮንን ሻለቃ ጉዊን ድንበሩን ከስምምነቱ ውጭ ብቻውን ሄዶ ከመከለሉም በላይ አፄ ምኒልክ ተገድደውም ቢሆን የፈረሙትን ካርታ አዛብቶ ኢትዮጵያን እየጎዳ ችካል ቸከለ። ይህንንም ሻለቃ ጉዊን ከተሰጠው ሥልጣን በላይ ሄዶ መሥመሩን በማዛባት ከኢትዮጵያ መሬት እንደወሰደ በራሱ ሪፖረት ላይ በግልፅ ሳይደብቅ ጽፏል። እንግሊዞችም 1902 የተፈረመበትን ካርታ ጥለው በችካሉ መሠረት 1903 አዲስ ካርታ በመሥራት እነርሱ ከፈረሙበት በኋላ አፄ ምኒልክን ለማስፈረም ቢሞክሩም ከስምምነት ውጭ ለተቸከለው የጉዊን ክለላ ዕውቅና በመንፈግ ሳይፈርሙበት ቀርተዋል። የትግሬው ዘረኛ ቡድን አፄ ምኒልክ፣ አፄ ኃይለሥላሴና ደርግ የጉዊንን መሥመር ተቀብለዋል እያለ የሚያላዝነው ይህንን የመሰለውን ሐቅ በመካድ ነው። ይህንንም ዓይን ያወጣ የወያኔን ቅጥፈት አዴኃን ብቻ ሳይሆን ሰኞ 19 ኖቬምበር 2007 (...) ሱዳን ትሪቢዩን የተባለ ጋዜጣም ድንበሩን አስመልክቶ የሱዳን መንግሥት ከቀደምት የኢትዮጵያ መንግሥታት ጋር የነበረው ግንኙነት ቀና አልነበረም። በድንበሩ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የመጀመሪያው ፈቃደኛ መንግሥት ገዥው የኢሕአዴግ መንግሥት ብቻ ነው በማለት መሥክሮበታል።
ጥሪ፦     
ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራትም ጭምር፣ ይህ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ በሀገር ከሃዲው የትግሬ ዘረኛ ቡድ ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወለጋና ከኢሊባቡር ክፍለ ሀገሮች ተቆርሶ ለሱዳን የሚሰጠው ለም መሬት የክፍለ ሀገራት ተወላጆቹ መሬት ብቻ አይደለም፤ የአንተም የኢትዮጵያዊው መሬት እንጅ። በመሆኑም አዴኃን ይህንን በባንዳ ልጆች የተጋረጥብንን ኢትዮጵያን የማጥፋት ታላቅ አደጋ ለመቀልበስ ስንል ያሉንን ጥቃቅን ልዩነቶች ወደጎን በመተው፣ ከምንጊዜውም በላይ እጅ ለእጅ ተያይዘንና ያለንን አቅም ሁሉ አስተባብረን በመነሳት የዜግነት ግዴታችን እንድንወጣ አስቸኳይ ጥሪውን ያስተላልፋል።ዳሩ ክልተጠበቀ፣ መሀሉ ዳር ይሆናልእንደሚባለው የትግሬውን ዘረኛ ቡድን በተባበረ ክንድ ዛሬውኑ ካላስወገድነው በስተቀር እናት ሀገራችን ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዕኩይ ተልዕኮው የድንበር መሬቶችን እየቆረሰ ለጎረቤት ሀገራት በመስጠት ብቻ ያቆማል ብሎ ማሰብ ፍፁም የዋህነት ነው።
ለመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ኃይልና የኢሕአዴግ ደጋፊዎች፣ እናንተ የምትደግፉት ሀገር አጥፊው የትግሬ ዘረኛ ቡድን አባቶቻችን ደረታቸውን ለጦር፣ እግራቸውን ለጠጠር ሰጥተው በደማቸው ያቆዩአትን ይህችን ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገራችንን እያጠፋት እንደሆነ ለእናነተ የተሠወረ አይደለም። ይህንን ሀገር የማጥፋት ወንጀል የሚፈፅመው ደግሞ እናንተን በመሣሪያነት በመጠቀም ስለሆነ ይህንን ተገንዝባችሁ አሁኑኑ ከሕዝባችንና አደጋውን ለመቀልበስ ከሚታገሉ ኃይሎች ጎን በመቆም ሀገራችሁን እንድትታደጉ ስናሳስብ፣ ጥሪያችን ችላ በማለት ለሀገር አጥፊው ቡድን ተባባሪነታችሁን ከቀጠላችሁበት ግን ታሪክና ሕዝብ ይቅር እንደማይላችሁ በጥብቅ ልናስጠነቅቃችሁ እንወዳለን።
ለብአዴን አባላት፦እሣት አመድ ይወልዳልእንደተባለው ካልሆነ በስተቀር፣ አባቶቻችሁ ኢትዮጵያን ከሚያጠፋ ጠላት ጋር ተባብረው እናት ሀገራቸውን አላጠፉም፤ ይልቁንም ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው የታፈረችና አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለእናንተ አስረከቧችሁ እንጅ። እናንተ ግን የጀግኖች አባቶቻችሁ የባሕሪ ልጆች መሆን አቅቷችሁና አደራቸውን በልታችሁ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና አማራን ለማጥፋት ቆርጦ ለተነሳው የትግሬ ዘረኛ ቡድን አሽከር ሆናችሁ እናት ሀገራችሁንና ወገናችሁን እያጠፋችሁ ነው።ለእንጀራየ፣ ለልጆቼና ለቤተሰቦቼ ስል ወይም ተገድጀ ነው ይህንን የማደርገውየሚለው ውሃ የማይቋጥር ምክንያት እንደማያዋጣችሁ አውቃችሁ የጋራ ሀገራችንንና ወገናችንን ለመታደግ አብራችሁት እንደትቆሙ አዴኃን ከልብ የመነጨ የሀገር አድን ጥሪ ያቀርብላችኋል።
ወንድም ለሆነው የሱዳን ሕዝብ፦ የኢትዮጵያና የሱዳን ሕዝብ ለብዙ ሺህ ዘመናት ከአንድ ወንዝ ከተቀዳ ውሃ እየጠጣ፣ በመከባበር ላይ በተመሠረተና በመልካም ጉርብትና አንዱ ለሌላው የችግር ጊዜ ደራሽ ሆኖ የኖረ ወንድማማች ሕዝብ ነው። ነገር ግን ዛሬ የትግሬው ዘረኛ ቡድን በሀገር ውስጥ የሚገኙ ነገዶችን እርስ በእርሳቸው ከማናከስ አልፎ የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይም የአማራውን ነገድ ወንድም ከሆነው የሱዳን ሕዝብም ለማናከስ ቆርጦ የተነሳ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕውቅና ውጭ የተፈረመን የድንበር ስምምነት እንዳይቀበል በጥብቅ እናሳስባለን።
በመጨረሻም የዓለም ምንግሥታትና ዓለምአቀፍ ሠላም ወዳድ ሕብረተሰብም የወያኔ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ፈፅሞ እንደማይወክልና አሁን ከሱዳን መንግሥት ጋር በድብቅ የተፈራረመውንም የድንበር ስምምነት ንቅናቄያችን አዴኃን እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማያውቁት ተገንዝበው ስምምነቱ አሁንም ይሁን ወደፊት በሁለቱ ሀገራት ሕዝብ መካከል የሚፈጠረውን ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለስምምነቱ ዕውቅና እንዳይሰጡና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ይህንን ሤራ እንዲቃወሙ አዴኃን ጥሪውን ያስተላልፋል።
በደም የተረከብናትን ሀገር በደም እንጠብቃታለን!!


የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ

   Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment