Thursday, May 28, 2015

ምርጫ ቦርድ የአስቂኙን ምርጫ ውጤት ይፋ አደረገ * ኢሕአዴግ 100% አሸነፈ አለ * ምንም አይነት ተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ወንበር አላገኘም

ኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ የዘንድሮውን አሳፋሪ ምርጫ 100% ማሸነፋቸውን ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ገለጸ:: ምንም አይነት ተቃዋሚ ፓርቲ በፓርላማው ውስጥ መቀመጫ እንዳላገኘም ተገልጹዋል::
የገዢው ፓርቲ መሳሪያና ገለልተኛ ያልሆነው ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ኢህአዴግ አዲስ አበባ ላይ ከ23 መቀመጫዎች ኢህአዴግ 23ቱንም መቀመጫዎች አግኝቷል።

– ከትግራይ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ31 መቀመጫዎች ውጤት ህውሃት/ኢህአዴግ 31 መቀመጫዎችን
– ከአማራ ክልል ከደረሱት የ107 መቀመጫዎች ውጤት ብአዴን/ኢህአዴግ 107 መቀመጫዎች
ከኦሮሚያ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ150 መቀመጫዎች ውጤት ኦህዴድ/ኢህአዴግ 150 መቀመጫዎችን
– በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ16 መቀመጫዎች ውጤት ኢሶዴፓ 16 መቀመጫዎችን
– ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከደረሱት የሰባት መቀመጫዎች ውጤት ሰባቱንም ቤጉዴፓ;
– ከደቡብ ክልል ከደረሱት የ95 መቀመጫዎች ውጤት ዴኢህዴን/ኢህአዴግ 95 መቀመጫዎች፣
– በጋምቤላ ክልል ጋህዴፓ ከሶስት መቀመጫዎች ሶስቱንም፣ በሀረሪ ክልል ሀብሊ ከ2 መቀመጫዎች አንዱን ሲያገኝ አንዱን ኦህዴድ/ኢህአዴግ፣
– በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሁለቱ መቀመጫዎች አንዱን ኦህዴድ/ኢህአዴግ ቀሪውን ሶህዴፓ አግኝተዋል
– ከአፋር ክልል ከደረሰው ከደረሰው የስድስት መቀመጫዎች ውጤት አብዴፓ ስድስቱንም መቀመጫ አግኝቷል።


በአሳፋሪነቱ የሚጠቀሰው የዘንድሮውን ምርጫ የአውሮፓ ሕብረት; የአሜሪካ መንግስትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ ሲሉ አውግዘውታ:: ተቃዋሚዎችም የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41775

No comments:

Post a Comment