Sunday, May 3, 2015

“እንከን የለሹ” የምርጫ ዝግጅት በትግራይ እንዲህ ባለ “እንከን የለሽ” ሁናቴ እየተከናወነ ነው፡

እንግዲህ የትግራይ ክልል ምርጫ ቦርድ ሐላፊዎች፣ አስፈፃሚዎች በየገጠሩ ህዝቡን እየሰበሰቡ “ንቧ እቺ ናት፣ እርሷ ላይ “X” የምታደርጉት፡፡ ሌሎች ምልክቶች ትናንት ሲያርዷችሁ፣ ሐውዜን ላይ ቦምቦች ሲያዘንቡባችሁ የነበሩት የጠላቶቻችሁና መቐለን ባግዳድ ማድረግ የሚሹ አሸባሪ ሐይሎች ምልክት ነው፡፡ ሁላችሁም አንዳንድ ስዕል ወደቤታችሁ ውሰዱና በደምብ አጥኑት፡፡ እላዩ ላይ X ማድረግ ተለማመዱ፡፡ ቀኑ እየደረሰ ነው፡፡ “
“ሌሎች ያልመጡትን በተለይም ወጣቶች ይህንን በደምብ አስረዷቸው፣ ተሳስተው ከጠላቶች ጋር እንዳያብሩ ምከሯቸው፡፡ ቄሶችም የነፍስ ልጆቻችሁን ይህንን እንዲመርጡ ማሐላ አስገቧቸው፤ እምቢ ካሉም ገዝቷቸው፣ አውግዛችሁም የነፍስ አባትነታቹ አቁሙ፡፡ “
“ሌላ ፓርቲን የመምረጥ ዝንባሌ ያሳየ ማንኛውም ገበሬ የመስኖ ውሐ ካለ ከውሐው እንዳይጠቀም፣ ቢታመም እንዳትደርሱት፣ ቢሞትም እንዳትቀብሩት፣ ከማንኛውም ማሕበራዊ ኑሮ እንዲገለል፡፡”
“ደግሞ ‘እቺ ንብ ለናንተ ማር ሰጠች እንጂ እኛንስ ከመንደፍ ያለፈ ምንም አልፈየደችልንም’ የምትሉ እንዳላችሁ ሰምተናል፣ ራዕዩ ሲገለፅላችሁ እናንተም ማሩ መቁረጥ ትጀምራላችሁ፡፡
ግንቦት 16 ላይ እንገናኝ፡፡ እነዚህን ስዕሎች ላይ X ማድረግ በተለማመዳችሁት መሰረት ያው “X” ማድረግ ነው፡፡”
እንከን የለሹ “የምርጫ ስልጠና” በትግራይ እንዲህ ባለ ሁኔታ እየተካሄደ ነው፡፡ ምርጫ አስፈፃሚውም “እንከን የለሽ ገለልተኛነቱ”ን እንዲህ ባለ “እንከን የለሽ ሁኔታ” አስመስክሯል፡፡
http://satenaw.com/amharic/archives/6688

No comments:

Post a Comment