ምርጫ 2007
ተጠናቆ ተወዳዳሪም አወዳዳሪም የሆነው ህወሓት ይፋ ውጤት እስኪገልጽ እየተጠበቀ ነው። ሁሉ በእጁ ነውና ባለሥልጣኖቹ ምን ዓይነት
ውጤት እንደሚስማማቸው እስከሚነግሩን ጥቂት ቀናት ይወስዱ ይሆናል። ከፈለጉ ሁሉን የፓርላማ ወንበሮች ሊወስዷቸው ይችላሉ፤
ካሻቸው ደግሞ ጥቂቱን ለተቃዋሚዎች ሊሰጡ ይችላሉ። ወሳኞቹ እነሱ ናቸው። በዚህ የፓርላማ ወንበሮች እደላ የኢትዮጵያ ሕዝብ
ድምጽ አንዳችንም ሚና የለውም።
ምርጫ
የሕዝብ የሥልጣን ባላቤትነት ማረጋገጫ ከሆኑ አቢይ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት አንዱ መሆኑ የታወቀ ነው። ሆኖም ግን ነፃ ተቋማት
በሌሉበት፤ በአምባገነኖች አስፈፃሚነት የሚደረግ ምርጫ የመራጮች ነፃ ፍላጎት መግለጫ በመሆን ፋንታ የገዢዎች ሥልጣን ማረጋገጫ
መሣሪያ ይሆናል፤ ከአገራችን እየሆነ ያለውም ይህ ነው።
የዘንድሮው
ምርጫ 2007 ከዚህ በፊት ከነበሩ በባሰ ለአፈና የተጋለጠ የነበረ መሆኑ ከጅምሩ በግልጽ የታየ ጉዳይ ነበር። በአንድነትና
በመኢአድ ፓርቲዎች ላይ አገዛዙ የወሰደው የግፍ እርምጃ የዚሁ የምርጫ ዘረፋ ስትራቴጂ አካል ነበር። ከዚያ በተጨማሪም መራጮች
እውነተኛ ፍላጎታቸውን በነፃነት መግለጽ እንይችሉ ዘርፈ ብዙ ጫናዎች ሲደረግባቸው ቆይቷል። የተወዳዳሪ ፓርቲዎች አባላት
እንደተፎካካሪ ሳይሆን እንደጠላት ሲሳደዱ፣ ሲታሰሩ፣ ሲደበደቡና ሲገደሉ ሰንብቷል። በምርጫው ሰሞንና በዕለቱ በተለይ ከተሞች
በባዕድ ጦር የተወረሩ መስለው ነበር። ይህ ሁሉ ስነልቦናዊና አካላዊ ተጽዕኖ ታልፎ የተሰጠው ድምጽ ቆጣሪው ራሱ “ተወዳዳሪ ነኝ”
ባዩ ህወሓት ነው።
በእንዲህ
ዓይነት ምርጫ መሳተፍ ትርፉ “በሕዝብ ድምጽ ተመረጥኩ የማለትን እድል ለአምባገኑ ህወሓት መስጠት ነው”፤ “ለዓለም ዓቀፍ
ማኅበረሰብም የተምታታ መልዕክት ማስተላለፍ ነው”፤ ”ለህወሓት ተጨማሪ ገንዘብ ማግኛና የኢትዮጵያን ሕዝብ መከራ ማራዘሚያ ነው“
በሚል በዚህ ምርጫ ላይ ማዕቀብ እንዲደረግ አርበኞች ግንቦት 7 ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል። በርካታ ወገኖቻችን
የምርጫ ካርድ ቢያወጡም የደረሰባቸውን ጫና ተቋቁመው በምርጫው ባለመሳተፍ ላሳዩት ጽናት አርበኞች ግንቦት 7 አድናቆቱን
ይገልፃል።
ህወሓት
በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የምርጫ ጉዳይ እና የምርጫ ፓለቲካ ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳን ተጨማሪ
ማስረጃ ለሚፈልጉ ግንቦት 16 ቀን 2007 መጥቶላቸዋል። አሁን ከፊታችን የተደቀነው ጥያቄ የሚከተለው ነው – አገራችን
ከህወሓት አፈና ነፃ ለማውጣት ያለን አማራጭ መንገድ ምንድነው?
አርበኞች
ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ህወሓት ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ የሚወርደው ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽን
ባቀናጀ ሁሉገብ ትግል ነው ብሎ ያምናል። በዚህም መሠረት ለሁለቱም የትግል ዘርፎች ተስማሚ የሆኑ አደረጃጀቶችን አዘጋጅቷል።
ሕዝባዊ
እምቢተኝነት፣ ታጋዩ ከመኖርያ ወይም ከሥራ ቦታው ሳይለቅ በህቡዕ የሚከናወን ትግል ነው። ሕዝባዊ አመጽ ደግሞ ከመኖሪያና ሥራ
ቦታ ለቆ መንቀሳቀስን ይጠይቃል። ሁለቱም የትግል ዘዴዎች የህወሓትን ህጎች በመቃወም የሚደረጉ ናቸው። ሁለቱም የትግል ዘዴዎች
ድርጅት፣ ዲሲሊንና ጽናትን ይጠይቃሉ። ለድላችን ሁለቱም የትግል ዘርፎች እኩል ዋጋ አላቸው። እናም ከዛሬ ጀምሮ እያንዳንዱ
ኢትዮጵያዊ እንደዝንባለውና አቅሙ በሚመቸው የትግል ዘርፍ ይሳተፍ። ሕዝባዊ ኃይልን መቀላቀል የቻለ ይቀላቀል፤ ያልቻለው
በያለበት ተደራጅቶ በሕዝባዊ እምቢተኝነት ይታገል።
በየመኖሪያ
ሠፈሩና በሥራ ቦታዎች የሚቋቋሙ የአርበኞች ግንቦት 7 ማኅበራት በርካታ ሥራዎች አሏቸው። ከሁሉ አስቀድሞ ድርጅትን ማጠናከር
የሁላችንም ድርሻ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም፤ እናም ትኩረታችን እዚያ ላይ እናድርግ። እያንዳንዳችን ከሚመስሉንና ከምናምናቸው ጋር
ተነጋግረን እንደራጅ፤ ወያኔ የሸረሸረብንን በራስ መተማመን እና የእርስ በርስ መተማመንን መልሰን እንገንባ። ውስጥ ውስጡን
ጠንካራ አገራዊ ኅብረት እንፍጠር፤ የዕለት ተዕለት ተግባሮቻችን ደግሞ አካባቢያዊ ይሁኑ።
ድርጅታችንን እያጠናከርን ወያኔን
ከሁሉም አቅጣጫ እንሸርሽረው እንገዝግዘው። በዚህ መንገድ በሚደረግ ሕዝባዊ ትግል የሚገኝ ድል ፈጣን ከመሆኑን በላይ የድሉ
ሕዝባዊነት ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ይሆናል።
ስለሆነም
እያንዳንዱ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ታጥቆ እንዲነሳ፤ ወደ ተግባራዊ ትግል ፊቱን እንዲያዞር አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41754
No comments:
Post a Comment