Monday, May 11, 2015

የጋምቤላ ነዋሪዎች መንግስት በታጠቁ አካላት እያስጨፈጨፈን ነው አሉ !!



በጋምቤላ ክልል፣ መጃንግ ዞን፣ ጎደሬ ወረዳ የሚኖሩ ዜጎች በመንግስት በተቀነባበረ ሴራ ጭፍጨፋ እየደረሰባቸው እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በተለይ ከግንቦት 2006 ዓ.ም ጀምሮ 400 ያህል ነዋሪዎች እንደተገደሉ የገለጹት ነዋሪዎች መንግስት የእርስ በእርስ ግጭት ለማስመሰል ቢሞክርም ችግሩ በመንግስት የተቀነባበረ እንደሆነ እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡
¨
‹‹የአብዛኛዎቹ ነዋሪዎች እርሻ ለገዥው ፓርቲው ካድሬዎች በመስጠት እኛ ከቦታችን እንድንፈናቀል ጥረዋል፡፡

አንወጣም ስንል ግን በግድ እንድንወጣ የተላከብን ጨፍጫፉ ነው›› ሲሉ የአካባቢው ነዋዎች በስልክ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በግልጽ ባልታወቁ ነገር ግን እነሱ ሚሊሻዎች እንደሆኑ በሚገምቷቸው 10 ያህል ሰዎች እንደተደገደሉ ነገር ግን ከስድስቱ በስተቀር የሌሎቹን ሰዎች አስከሬን ማንሳት እንዳልቻሉ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ 


ነዋሪዎቹ አክለውም ‹‹መንግስት በጭፍጨፋው ላይ እጄ የለበትም ቢልም ህዝቡ ሲማረር ይወጣል በሚል እያስጨፈጨፈን ይገኛል፡፡

 በርካታ ወታደርና ፖሊስ ቢኖርም ጭፍጨፋውን ለማስቆም ጥረት አለማድረጉ መንግስት ከበስተጀርባው እንዳለ እንድናምን አድርጎናል፡፡›› ብለዋል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41294

No comments:

Post a Comment