Tuesday, May 19, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተገለፀ


የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አሁንም እየታደኑ እየታሰሩ ነው፡፡ በትናንትናው ዕለት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ተስፋዬ በፖሊስ ታድኖ ተይዟል፡፡ በአሁኑ ወቅት አራዳ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች በሚሊሻዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ በቃሉ አዳነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ታዛቢዎቹ ‹‹ከአሸባሪ ፓርቲ ጋር አብራችሁ እየሰራችሁ ነው›› እየተባሉ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ የገለጹት አቶ በቃሉ ቀሪዎቹን ‹‹ከአሸባሪ ፓርቲ ጋር ሲሰሩ አገኘናቸው ብለን እንከሳችኋለን›› እያሉ እያስፈራሯቸው ነው ብለዋል፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የምትገናኙበት ነው በሚልም ስልካቸውን እንደሚነጠቁ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን በየወረዳው ከብርሸለቆ የሰለጠኑ 150 ሚሊሻዎች ተመድበው የተቃዋሚ በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን፣ ታዛቢዎችንና ህዝቡን በማስፈራራት ላይ እንደሚገኙ አቶ በቃሉ ገልጸዋል፡፡ አቶ በቃሉ አክለውም ‹‹በየ ወረዳው የተመደቡት ሚሊሻዎች ስራቸው ህዝቡን ማስፈራራትና ማሸበር ነው፡፡ ይህንም የሚያደርጉት ምንም ነገር ሳይከሰት ጥይት ወደ ላይ በመተኮስ ነው፡፡ በዚህ ሂደት በተባባሪ ጥይት የሞተ ሰውም አለ›› ብለዋል፡፡


በተመሳሳይ በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ሳንቃ ከተማ ላይ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ ያረጋል ፈንታው፣ ሁሴን እንድሪስና ዝናቡ ጋሊስ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ዕጩዎች በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በሰሜን ወሎ ዞን ሚሊሻዎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ድብደባ እንዲፈፅሙ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸውም አስተባባሪዎቹ ተገልጾአል፡፡ በዞኑ ካድሬዎች መራጩን ‹‹ኢህአዴግን እመርጣለሁ›› ብላችሁ ፈርሙ እያሉ እያስገደዱ እንደሆነ የገለጹት የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪዎች ‹‹ድምጼን የምርጫው ቀን ነው የምሰጠው›› የሚሉ መራጮችን ካድሬዎች ‹‹እኛን አትመርጡም ማለት ነው!›› እያሉ እየዛቱባቸው ነው ብለዋል፡፡

http://satenaw.com/amharic/archives/7053

No comments:

Post a Comment