Friday, May 22, 2015

ማይጨውም ተወጥራለች..! – አምዶም ገብረስላሴ

የህወሓት ጭንቀት በገጠርም በከተማም በከፍተኛ ደረጃ ደርሰዋል። ማይጨው ከተማም እንደሌሎች የትግራይ ኣከባቢዎች በክፍተኛ ውጥረት ትገኛለች።

በማይጨው ከተማ ያለው ውጥረት በማይጨው ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎችና በኮሌጁ ኣስተዳደር፣ በተማሪዎችና የከተማው ካድሬዎች፣ በካድሬዎችና በኑዋሪ ህዝብ መካከል ነው።

የውጥረቱ መነሻ “..ዓረና-መድረክ በከተማው ያለው ተቀባይነት ህወሓት ሊያሽንፋት ይችላል..” የሚል ድምዳሜ በዞኑና በከተማዋ ኣስተዳዳሪዎች ድምዳሜ ስላስደረሳቸው ነው። በማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተፈጠረው ውጥረት የህወሓት ካድሬዎች ከኮሌጁ ኣስተዳዳሪዎች በመሆን ተማሪዎቹ ኣንድ በኣብድ ወደ ኦፊስ በመጥራት ከዓረና-መድረክ ኣባልነት ውጣ…!፣ ከዓረናዎች ጋር ግንኙነት ኣለህ…!፣ ኣቋምህ ግልፅ ኣይደለም..!” የሚሉ ጥያቄዎ በማቅረብ “..ግለ ሂስ ኣድርገህ፣ ይቅርታ ጠይቀህ በሰላም መኖር ትችላለህ። ኣለበለዚያ ግን እኛ በስንት መስዋእትነት ያመጣነው ስልጣን በወረቀት የሚቀየር እንዳይመስልህ፣ ከምርጫ በሗላ በዚች ኣገር በሰላም የምትኖር እንዳይመስልህ..” እየተባለ ሲያስፈራሩት ውለዋል።

ይህ ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎች የማይጨው ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን መምህር ግርማይ ሓጎስ፣ ምክትል ዲን መምህር ዓፈራ ሲሆኑ ከካድሬዎች ደግሞ ሃፍቱ ጫሪ፣ መምህር ሚኪኤለ ኣበበና የማይጨው ከተማ ፕሮፖጋንዳ ሃላፊ ኣቶ ተሻለ ባይሩ ናቸው። የዚህ ውጤት ደግሞ “..እኛ የፈለግነው ፓርቲ ኣባል የመሆን፣ የመደገፍና የመምረጥ መብት ኣለን። የፈለጋቹ እርምጃ ልትወስዱ ትችላላቹ፣ እኛ ደግሞ በእምነታችን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁዎች ነን..” በማለት ኣንጀታቸው ኣሳርረው መልሶኣቸዋል።

በማይጨው ህዝብና ካድሬዎችም ተመሳሳይ ውጥረት ነግሶ ይገኛል። ካድሬዎች የህወሓት ድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ ህዝቡ ቀጭን ትእዛዝ በማስተላለፍ ሳይወድ በግድ እንዲወጣ ቢያደርጉትም ህዝቡ እየቀለደባቸውና እየተሳለቀባቸው ኣርፍደዋል። በሌላ ኣጋጣሚ ደግሞ የምርጫ ወረቀት ይዘው የተገኙ የቀበሌ ሴቶች የዓረና-መድረክ ኣባላት በማጋለጣቸው ምርጫ ቦርድም ወረቀቱ ኬት እንዳመጡት ቢጠይቋቸውም የከተማዋ ከንቲባ ኣቶ ተስፋይ ኪዳኑ በኣካል ተገኝቶ ነገሩ እንዲደፋፈን ኣድርጎታል።

ህወሓትየማይጨው ወጣቶች፣ የፖሊ ቴክኒክ ተማሪዎችና ኑዋሪ ህዝብ የህወሓት ራስ ምታት ሁኖበታል። ኣዎ..! ህዝብ የፈለገው ለውጥ ከማድረግ ማንኛውም ሃይል ኣይገታውም።

ነፃነታችን በእጃችን ነው..!

http://satenaw.com/amharic/archives/7124

No comments:

Post a Comment