Sunday, May 17, 2015

ህወሃትን መምረጥ ማለት ገዳይን መምረጥ ማለት ነው።

. ህወሃት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ያደረገ ድርጅት ስለሆነ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት ለትግራይ ሕዝብ እንኳን የማይራራ የትግራይ ወጣቶችን ያስፈጀ በመሆኑ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበሯን በማስደፈሩ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት ወጣት ኢትዮጵያውያንን ለባርነት የዳረገ ስለሆነ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት ኢትዮጵያውያንን አገር ጥለው እንዲሰደዱ ያደረገ በመሆኑ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት የሀገርና የሕዝብ ሀብት ዘርፎ ወደ ውጭ በማውጣት አገር ያደኸየ በመሆኑ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት በመግደልና በማሰር የሚያምን ፋሽስት ድርጅት በመሆኑ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት ጠባብና ዘረኛ ድርጅት በመሆኑ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት የአማራውን ነገድ ሕዝብ ዘር በማጥፋት የተሰማራ በመሆኑ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት በክርስቲያኑም ሆነ በእስልምናው እምነት ጣልቃ በመግባት ሁከት የፈጠረ በመሆኑ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት የኢትዮጵያን አንድነት የናደና ኢትዮጵያውያንን እንዳይተማመኑ በማድረጉ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት ሕገ-መንግሥቱን የጣሰ በመሆኑ መመረጥ የለበትም፤

. ህወሃት ሕግ አውጭ፤ሕግ ተርጓሚና ሕግ አስከባሪ ባለመሆኑ መምረጥ የለብንም፤

. ህወሃት በሕዝብ ተመርጦ ስልጣን ላይ ስለአልወጣና የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለማይወክል መምረጥ የለብንም፤

. ህወሃት ታሪክን ያዋረደና የካደ ድርጅት በመሆኑ ሊመረጥ አይገባውም፤

. ህወሃት የመደራጀት፤የመጻፍ፤የመሰብሰብ፤የመናገር፤በሀገር የመኖርን፤ሀብት የማፍራትን መብት በመግፈፉ ሊመረጥ አይገባውም፤

. ህወሃት በግድ አባል የማድረግና ከአባላቱ ውጭ ያለውን ሕዝብ የማይፈልግ በመሆኑ በምርጫ ካርድ ሊባረር ይገባዋል፤

. ህወሃት ምሊዮኖቹን  ያሠረ በመቶ ሽህ የሚቆጠሩትን የገደለ ወንጀለኛ ድርጅት ስለሆነ መመረጥ የለበትም።


እንደ አንድ ኢትዮጵያዊነቴ ህወሃት ከዚህ በላይ በጠቀስኳቸውና በሌሎችም ተጠቅሰው የማያልቁ ህልቆ መሳፍርት የሆኑ ፋሽስታዊ ድርጊቶቹ ሊመረጥ አይገባውም ብየ እየሞገትኩ ስለሆነ መራጩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቅርቡ በሚጀመረው የ2007 ምርጫ ህወሃትን ከጨዋታው ውጭ ማድረግ አለበት።ህዝቡ ማድረግ ያለበትን አድርጎ ህወሃት በተለመደው መንገድ ሄዶ የምርጫ ኮሮጆ እዘርፋለሁ ካለ ከዚያ በኋላ የሚሆነውን እናያለን።ሕዝቡ እነዚህን ሁሉ እያወቀ በማይረባ ጥቅማ ጥቅምና በህወሃት የውሸት ጋጋታ ተጭበርብሮ ህውሃትን ቢመርጥ አንድምታው የሚሆነው፦ በግልጽ ዝረፍ፤ግደል፤እሠር፤ደብድብ፤ከሀገር አሳደህ አስወጣን፤መሬታችን ሽጥ ለገፀ-በረከት አድል፤ድንበራችንና ሉዓላዊነታችን አስደፍር፤ልጆቻችንን ለባርነት አሳልፈ ስጥልን፤ዜግነታችን ግፈው ወዘተ ብሎ እንደወሰነ ህዝብ ስለሚታይ አስቀድመን ልናውቀው ይገባል። 

No comments:

Post a Comment