Sunday, May 17, 2015

በዓረና መድረክ የተደናገጠው ሕወሓት በትግራይ የተቃዋሚዎችን የምርጫ ፖስተሮች መቅደድ ጀምሯል

አምዶም ገብረስላሴ ከትግራይ እንደገለጸው

የዓረና መድረክ የእጩ ተወዳዳሪዎች ምስል የያዙ ፖስተሮች በህወሓት የወረዳ ካቢኔ ኣባላት፣ ካድሬዎች፣ ፖሊሶችና የኮብልስቶን በመስራት ላይ ያሉ ወጣቶችና በህፃናት ኣማካኝነት እየተቀደደ ነው። የምርጫ ህጉ የተወዳዳሪዎች ፖስተር መቅደድ በህግ የሚያስጠይቅና የሚያስቀጣ ቢሆንም ህወሓት ግን በህጉ ተገዢ ለመሆን ፍቃደኛ ልጦን ኣልቻለችም።

ህወሓት በተግባርዋ የህዝብ መሳቅያ ሁና ፍርሃትዋ ምን ያክል እንደሆነበ ትዝብት ላይ ወድቃለች። ይህ የህወሓት የፖስተር ቀደዳ ተግባር ለኮረጆ ቀደዳ እንደ የኣቋም መፈተኛ ልምምድ ሊታስብ ይችላል። እነሱ የፈለጉት ህገወጥ ተግባር ሲሰሩ እኛ ደግሞ የህዝባችን ልብ ፣ ድጋፍና ማገር እያገኘን እንጎመራለን።

ዓረና መድረክ እምዲህ ያስደነገጣቸው ምክንያት በመላ ትግራይ የምርጫ ታዛቢዎች መልምሎ ኣዘጋጅቶ በማቅረቡ ነው። ለታዛቢዎቻችን የእስራት፣ የማስፈራራትና ዛቻ በኣስተዳዳሪዎች እየደረሰባቸው ነው።


የፖሊስ ስራውና ሃላፊነቱ በኣግባቡ ኣለመወጣት ምርጫው ወዳልሆነ ኣቅጣጫ እየወሰደው ይገኛል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41439

No comments:

Post a Comment