ዛፍ በፍሬው ይታወቃል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያስተላለፈው ውሳኔ ሀገራችንና ህዝባችን ምን ያክል አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደገቡ ያሳያል፡፡ሲኖዶሱ በመንፈስ ቅዱስ ይመራል ቢባልም አንዴ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም፤ አንዴ አቶ አባይ ጸሀዮ ፤ሲያስፈልግም አቦይ ስብሃት እና አቶ በረከት ስምኦን እየተፈራረቁ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የጥፋት በትራቸውን እያሳረፉበት ይገኛሉ፡፡እንግዲህ የመንግስት ሰዎች በዚህ መልኩ እየተፈራረቁ ተጽዕኖቸውን ሲያሳርፉ በውስጡ የተሰገሰጉት የወያኔ ወኪል አባቶች ደግሞ ህዝቡ ተደራጅቶ መብቱን እንዳያስከብር ጊዜ ለማግኘትና ውስጥ ውስጡን ለሰላም የቆሙ በመምሰል በሽምግልና እና በጸሎት አማካይነት ይስተካከላል እያሉ ሲያታልሉ ቢቆዩም ዛሬ የመንግስትን አቋም ለማስፈጽም መቆማቸውን በግልጽ አሳይተዋል፡፡
የመግለጫው ይዘት ስናየው ለማደናገሪያ ያክል በውስጡ አንዳንድ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶችና የግዕዝ ቃላቶች ከመግባታቸው በስተቀር ወያኔ በየሦስት ወሩ እያሳተመ ለአባላቶቹ ከሚያሰራጨው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ውዳሴ መጽሔት ከሆነችው የአዲስ ራዕይ መጽሔት፤ በበረከት ሰምኦን በኩል ከሚለቀቀው የመንግስትን አቋም የሚተነትን ተብሎ በመሰለ ገብረህይወት እየተነበበ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከሚቀርበው ፕሮፖጋንዳ የተለየ አደለም፡፡ከዚህ መገመት የሚቻለው መንግስት አስቀድሞ ተዘጋጅቶበት መግለጫው በሲኖዶስ እንዲነበብ መደረጉን ነው፡፡ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪወስ በ1984 ዓ.ም በአቶ ታምራት ላይኔ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ መባረራቸው ያደባባይ ሚስጢር ሁኖ ሳለ ዛሬም በተለመደው ቅጥፈታቸው በገንዛ ፈቃዳቸው ጥለው ሸሽተዋል፣ስልጣኑን ለፈለጋችሁት ስጡት ብለዋል ተብሎ የተጻፈን ጽሁፍ የሲኖዶስ ውሳኔ ነው ብሎ ማውጣት ምን ያክል አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡ጳጳሱ ወታደር ያላቸው ይመስል የቅድስተ- ማሪያምን ቤተክርስቲይን በታንክና በመትረጌስ አስከብበው የተወሰኑ ካድሬ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ተብየዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያዘጋጁ ተደርጎ በተቀነባበረ ሴራ እንደተባረሩ እየታወቀ በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ ሲባል በተለይ አለም በቃን ካሉ መነኮሳት መስማት ምን ያክል አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡
ማቴ.7፤16-20 ” ጥሩ ዛፍ መጥፎ ፍሬ አያፈራም፡፡እንዲሁም መጥፎ ዛፍ ጥሩ ፍሬ አያፈራም፡፡ዛፍ ሁሉ በፍሬው ያታወቃል፡፡” ባለፉት 38 ዓመታት ወያኔ ያፈራቸው የክህደት ፍሬዎች እንዳይናቸው ብሌን እንዲንከባከቡ ከእግዚያብሄር የተረከቡዋቸውን የመንፈስ ልጆቻቸውን በመበተን ይህን አሳፋሪ ተግባር አሜን ብለው ተቀብለዋል፡፡ዛሬም ቢመሽም ቅሉ ፈጽሞ አልጨለመምና በተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያ ምክንያት ያላመናችሁበትን የፈጸማችሁ አባቶች የእግዚያብሔርን ቃል አስታውሱ፡፡ከቤተ-ክርስቲያንና ከምእምናን ጎን በመሰለፍ የእስልምና እምነት ተከታይ የሀይማኖት መሪዎች እንዳደረጉት እንንተም ለእምነታችሁ መከበርና ለቤተክርሰቲያናችሁ አንድነት ነገቢውን ዋግ ክፈሉ፡፡
ማቴ.10፤26-28 “ እንግዲህ ሰዎችን አትፍሩ፤ምክንያቱም የተሸፈን መገለጡ አይቀርም፤ተሰወረም መታወቁ አይቀርም፤በሹክሹክታ የሰማችሁትንም በከፍታ ቦታ ላይ በይፋ አስተምሩ፡፡ለእናንተ ለወዳጆቼ እንዲህ እላችኋለሁ፤ስጋን ከመግደል አልፈው ነፍስን መግደል የማይችሉትን ሰዎች አትፍሩ፤ ይልቁን ነፍስን እና ስጋን በገሀነም ሊያጠፋ ሚችለውን እግዚያብሄርን ፍሩ፡፡” ይላል የእግዚያብሄር ቃል፡፡
ሉቃ.13፤6-7 “አንድ ሰው በአትክልቱ ውስጥ የተተከለች አንዲት የበለስ ዛፍ ነበረችው፡፡ከዚያችም የበለስ ዛፍ ፍሬ አገኛለፉ ብሎ በተለያዩ ጊዜያት እየሄደ ቢሞክርም ምንም ፍሬ ሳያገኝ ቀረ፡፡ስለዚህ አትክልተኛውን ጠርቶ ከዚች ዛፍ ፍሬ ለማግኘት ሦስት አመት ሙሉ ተመላለስኩ፤ ግን ምንም ፍሬ አላገኘሁባትም፤አሁን ቁረጣት ስለምን የአትክልቱን ቦታ በከንቱ ይዛ ታበላሻለች አለው”፡፡ እንግዲህ ከዚህ ምሳሌ መረዳት ሚቻለው ባለፉት 21 አመታት ፍሬ ያልሰጡትን አቡነ ጳውሎስን እና አቶ መለስ ዜናዊን የአትክልቱ ቦታ ባለቤት በቁጣ ቢነቅላቸውም ከትፋጣቸው መማር የማይችሉት ደቀ- መዛሙርቶቻቸው እነ አቶ አባይ ጸሀዬ እና አቦይ ስብሀት አንዲሁም ሌሎች የወያኔ ቡችሎች በጥፋታቸው ቀጥለውበታል፡፡ይባስ ብሎ በእነሱ ግፍና መከራ በስደት ኑሮዋቸውን መግፋት ሳያናሳቸው ሽብርተኛ በመሆናቸው አቡነ መርቆሪወስ ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል ሲሉ “አቫይ ጸሀዬ” ነግረውናል፡፡ወያኔዎች መልካም ፍሬ ለማፈራት የማይችሉ ተሰጣቸውን ሀገርን የማስተዳደር ትልቅ ሀላፊነት በተጠናወታቸው የዘር ልክፍት ምክንያት ህዝቡን ለብጥብጥ፣ ለሞት፣ለችግር እና ለስደት ከመዳረግ በቀር ሌላ ነገር የለም፡፡ውድ ኢትዮጵያውያን የእግዚያብሄርም ቃል የሚነግረን ፍሬ የማያፈሩትን ዛፎች ቆርጦ መጣል እንደሚገባ ነው፡፡የሌሌች ሀገሮችም ተሞክሮ የሚያሳየን ያለ ሀይል አልለቅም ብሎ በግድ የተጣበቀብንን ካናሰር በኃይል ቆርጦ መጣልና ነጻነታችንን ማስመለስ ነው፡፡
Posted By Dawit Demelash
No comments:
Post a Comment