Saturday, January 5, 2013

   ህወሀት በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍና በደል

      የ “አማሮች ገለል በሉ ጉዳይ”: ታሪክ የማይረሳው ዋጋ ያስከፍላል:  ከአምደጺዮን

ሁሉም ነገር ገደብ ያስፈልገዋል። ኢትጵያዊ ትህትና ፣ ትዕግስት ፣ ይሉኝታ ፣ …… እና ሌሎች በመልካም ምግባርነት
የሚወደሱ ሰብአዊ ባህሪዎች መልካምነታቸው አጠራጣሪ ባይሆንም ልክ ፣ ገደብ እና ሚዛን ….. ከሌላቸው ግን ስሜት
አልባነትን ፣ ሙትነትን ፣ ፈሪነትን፣ ተሸናፊነትን፣ አጎብዳጅነትን …… ማመልከታቸው አይቀርም።
ዛሬ በሀገራችን በኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነት ከምንም በላይ አንገትን የሚያስደፋ ሆኗል። ኢትዮጵያዊነትን መግለፅ፣ የሚወዷትን
ሀገር በመለያነት መጠቀም ወይም ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት ማስከበሩ ቀርቶ መዘለፊያ ሆኗል፤ “ትምክህተኛ” ለሚል ዘለፋ
የሚዳርግ ፣ ለጥቃት የሚያጋልጥ ፣ ለእስር ፣ ለግድያ የሚያበቃ ፣ እንደ ሀገር አጥፊ ፣ እንደ መንግስት ጠላት እያስቆጠረ
አንቀጽ የሚጠቀስበት ከሆነም ሁለት አስርት አመታት እንደዘበት ነጉደዋል። ይህ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት
የማኮላሸት ስትራቴጂ ባለፉት የህወሀት የሀያ አንድ አመታት የስልጣንና የአገዛዝ ዘመን ዋነኛ የፖለቲካ ስልት እና ዒላማ ሆኖ
የህወሀትን ዕድሜ ለማራዘም ሁነኛ መሳሪያ ሆኖ አገልግሏል።
በዚህ በኩል በተለይ የአማራ ህዝብ የህወሀት ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ እንዲጋት ሲደረግ ቆይቷል።
ህወሀት የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ
ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል።
ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በህወሀት የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ
በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል። to continue reading on PDF click here    http://ethioforum.org/wp-content/uploads/2013/01/amaroch_gelel_belu.pdf
posted by Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment