Friday, January 11, 2013

እስራኤል ተጨማሪ ታዳጊዎች ለቀቀች

samuel alebachew
በእስራኤል አገር ታስረው ከሚገኙት ታዳጊዎች መካከል አራቱ መፈታታቸውን አቶ ሳሙኤል አለባቸው የኢትዮጵያ እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል ሊቀመንበር በተለይ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ አስታውቀዋል። አሁንም እስር ላይ የሚገኙት ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ አስር ታዳጊዎችን ለማስፈታት አስፈላጊው ሁሉ እየተደረገ መሆኑንንም አስታውቀዋል።
አቶ ሳሙኤል በጽሁፍ በላኩት መልዕክት እንዳስታወቁት ከጎንደር አስኮብላዮች ወደ ሲና በረሃ በመውሰድ ለከፍተኛ እንግልትና ህሊናን የሚፈታተን ስቃይ ከዳረጓቸው ታዳጊዎች መካከል እስራኤል መድረስ የቻሉት እዚያ ሲደርሱ የገጠማቸው እስር ነበር። በተለይም እድሜያቸው ከአስራስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ከታወቀ በኋላ እርሳቸው የሚመሩት ድርጅትና የወገኖቻቸው ስቃይ እረፍት የነሳቸው አገር ወዳዶች ባደረጉት ትብብር ቀደም ሲል ስድስት ታዳጊዎች ከእስር ተለቅቀው ነበር።
ተጨማሪ አራት ታዳጊዎች መፈታታቸውን ያስታወቁት አቶ ሳሙኤል፣ ቀደም ሲል ከእስር ከተለቀቁት ስድስት ታዳጊዎች ጋር በመሆን በ29/12/2012 የመጀመሪያውን ሰንበት (ቅዳሜ) ከወገኖቻቸው ጋር በጋር ለማሳለፍ ችለዋል። በማያያዝም በእስር ላይ የሚገኙ አስር የሚደርሱ ታዳጊዎች በተመለከተ “… ከእስር ቤት እንደሚገኙ የተነገሩን እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑና ቁጥራቸው ከአስር የማያንሱ ታዳጊዎች በተመለከተ ከእስር የሚፈቱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ተገቢው ጥረት እየተደረገ ነው” ብለዋል።
የሲና በረሃን በሚያቋርጡበት ወቅት የሰውነት ክፍላቸውን በመዘረፍ፣ በመደፈር፣ በድብደባና አሰቃቂ ስቃይ በኋላ ከሞት ተርፈው እስራኤል የገቡት ወገኖች ለእስር መዳረጋቸው፣ በበረሃ ውስጥ የታሰሩበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑና በታሰሩበት የሚደረግላቸው እንክብካቤ አስመልክቶ መረጃው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ይዘት እንዲይዝ በማድረግ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል
በ11/01/2013 ዓም አቶ ሳሙኤል አለባቸው የሚመሩት ድርጅት ይፋ ያደረጋቸው ታዳጊዎች ስም ዝርዝር በእድሜና በትውልድ ስፍራ በመለየት ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል።
ቀደም ሲል ኮሚቴው ያገኛቸው
ተቁ
ስም
እድሜ
የመጣችበት ክ/ሀገርና ልዩ ቦታ
መግለጫ
1
ዘርፌ ጌዴ እንደሻው
14
ጎንደር /ደባርቅ/

2
ለቄ ደጀን መለሰ
15
ጎንደር /ደባርቅ/

3
ባንቺ ባዜ በላይ
15
ጎንደር /ማክሰኝት ወረዳ/
ልዩ ለፍሬው ባህር ግንብ
4
ወደር ገብሬ ጫኔ
16
ጎንደር /ባሪ ግንድ/

5
ገበያነሽ ተስፋ አማረ
14
ጎንደር /ማክሰኝት ወረዳ/
ልዩ ቦታ 50 ፍጭ
6
አለምወርቅ ሲሳይ የኔነህ
14
ጎንደር /አጅሬ/

ቀሪዎቹ 4 ታዳጊዎች ማለትም በሁለተኛው ዙር ፍለጋ የተገኙና መረጃቸው ተሟልቶ የተላከ የሚከተሉት ናቸው።
ተቁ
ስም
እድሜ
የመጣችበት ክ/ሀገርና ልዩ ቦታ
መግለጫ
7
ሸዋዬ ሹመት አድባያቸው
15
ደባርቅ

8
ድንቄ መብራት አድባያቸው
14
ደባርቅ

9
ወርቅዬ ማሞ ጌጤ
14
ደባርቅ

10
ስለእናት ጥላዬ ቦጋለ
16
ደባርቅ

(ፎቶ: አቶ ሳሙኤል አለባቸው አድማሱ የኢትዮጵያ እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል ሊቀመንበር)

   Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment