Sunday, January 6, 2013

በአራት ኪሎ ካምፓስ የተነሳው የብሔር ግጭት

       በአራት ኪሎ ካምፓስ የተነሳው የብሔር ግጭት

ግጭቱ የተቀሰቀሰው አንድን ብሔር የሚያንቋሽሽ ጽሑፍ በቤተ መጻሕፍት፣ በመመገቢያ ካፌው፣ በመፀዳጃ ቤትና በዶርሞች አካባቢ ተጽፎ በመገኘቱ እንደሆነ የዩኒቨርሲቲው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ነፃነት ይልማ ተናግረዋል፡፡
ሐሙስ ጠዋት ሁኔታው እጅግ ተባብሶ በድንጋይና በዱላ ድብድብ ሲጀመር፣ የፌዴራል ፖሊስ በአካባቢው በፍጥነት በመገኘት ችግሩን ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደርግ፣ ተማሪዎቹ ፖሊስ ወደ ግቢው እንዳይገባ በድንጋይ ተከላክለዋል፡፡
በመሆኑም የፌዴራል ፖሊስ አድማ በታኝ ኃይል በአስቸኳይ ወደ አካባቢው
እንዲደርስ ተደርጓል፡፡ በመጀመሪያ የደረሰው አድማ በታኝ ኃይል አስለቃሽ ጭስና የፕላስቲክ ጥይት ተኳሾችን የያዘ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ኃይል ባልታወቀ ምክንያት ዕርምጃ እንዳይወስድ በማድረግ ሌሎች ቆመጥ የያዙ አድማ በታኞች በአካባቢው እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡ አድማ በታኝ ኃይሉ ወደ ግቢው ከገባ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ዩኒቨርሲቲው በጩኸት ለረጅም ደቂቃዎች ተደባልቋል፡፡
ከዚህ በኋላ በተለያዩ ተሽከርካሪዎች የተጐዱ ተማሪዎችን ወደ ሕክምና ተቋማት ማጓጓዝ የተጀመረ ሲሆን፣ ሌሎቹ ዋና ተጠርጣሪ የተባሉት ደግሞ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ ሰባት የሚሆኑ ተማሪዎች በከፍተኛ ጉዳት ሳቢያ በሕክምና ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ጉዳቱ የደረሰባቸውም በዕርስ በርስ ግጭት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከሰባቱ ተማሪዎች አንዱ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡ ሁለቱ ደግሞ መጠነኛ ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ተሰምቷል፡፡
http://www.ethiopianreporter.com
posted by Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment