Saturday, January 26, 2013


የኢሳት ቀን በሳንድሽን ኖርዌይ ካምፕ ውስጥ ተከበረ

ጥር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ተነሳሽነት ስለ ኢሳት አላማ ለ ኖርዌጅያን ማህበረሰብ ፣ በ ሳንድሽን አካባቢ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በሙሉ ለማሳውቅ እና ኢሳትንም እንዲደግፉ ለማድረግ የኢሳት ቀን በሚል ያዘጋጁት በአል መከበሩን ገልጸዋል።
በእለቱም በሳንድሽን ለሚኖሩ ኖርዊጅያን የተለያዩ የፖለቲካ ተወካዮች ፣ የስደተኞች አስተማሪዎች በሙሉ ስለ ኢሳት የሚገለጽ በራሪ ወረቀት በማዘጋጀት እንዲያውቁ ፣ በኢሳት ቀን ፕሮግራም እንዲንገኙ፣ እና እንዲደግፉ መደረጉን ገልጸዋል።
እኤአ ጃንዋሪ 24 ቀን 2013 በተከበረው በአል ላይ ለተገኙት በሙሉ ስለ ኢሳት ገለጻ መካሄዱን ኢትዮጵያውያኑ በላኩት ዘገባ አመልክተዋል።

Posted By.Dawit Demelash (sandnessjøen)

No comments:

Post a Comment