ወታደራዊ ጥቃቱ በአብደራፊም ቀጥሏል |
Written by Administrator | |
Friday, 04 January 2013 04:12 | |
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት በአብደራፊ ቀጥሏል።
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተሰማራው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የተያያዘውን ሕዝባዊ የአርበኝነት ትግል ለማፋፋም እየወሰደ ያለው ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃና ሕዝብን የማንቃት፣ የማደራጀትና የማነሳሳት የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ግንባሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሕዝብ አለኝትነቱንና የሀገር መከታነቱን እየመሰከረ ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በጠላት ላይ የሚያደርሰውን ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻውን አጠናክሮ በመቀጠል በታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ.ም አብደራፊ ሸሪፍ መሃመድ ልዩ ስፍራው ደዋል በተሰኘው አካባቢ ከወያኔ ታጣቂ ሚሊሻ ጋር ባካሄደው ውጊያ 7 ታጣቂ ሚሊሻዎችን ግድሎ 4 በማቁሰል የግንባሩ ሰራዊት አንፀባራቂ ድል ተቀዳጅቷል።
ይህን ተከትሎም በስጋትና በፍርሃት የተዋጠው አምባገነኑ የወያኔ ገዥ ቡድን በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የሚደርስበትን ጥቃት ለመመከት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የልዩ ሃይልና የመከላከያ ሰራዊት በቦታው ለማስፈር መገደዱ ታውቋል።
አንዳንድ ጥቃቱ በተፈፀመበት አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደገለጹት በመሳሪያና በወታደር ብዛት ተከልሎ ሀገርንና ሕዝብን እየገደሉ የአምባገነናዊ ስርዓት እድሜን ለማራዘም ወያኔዎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ሙጥኝ ካሉበት የስልጣን ማማ ላይ ከመወገድ ሊያድናቸው እንደማይችል ገልፀው ይልቁንም በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ተሰቅሎ ለከት የለሽ ግፍና በደል እያደረሰ የሚገኘውን አምባገነኑን የወያኔ ገዥ ቡድን ለማስወገድ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የጀመረውን የትጥቅ ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥልና ነዋሪዎቹም በሚደረገው የአርበኝነት ትግል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም ጨምረው ገልፀዋል።
|
No comments:
Post a Comment